መስቀል ማለት

·        በብሉይ ኪዳን ዘመን፤ በእስራኤል ዘንድ ሰው በድሎ ወይም ጥፋት አጥፍቶ ከተገኘ፤ የሞት ፍርድም ከተፈጸመበት በኋላ፤ አስከሬኑን በእንጨት መስቀል ወይም ዛፍ ላይ በማንጠልጠል  ለህዝብ ለማስጠንቀቂያ ወይም ማስተማሪያ ይሆን ዘንድ ይጠቀሙበት ነበር። ነገር ግን እስራኤላዊያን ሰውን በስቅላት አይገድሉም ነበር ። (ዘዳ 21፤21-23 ኢያ 10፤26)
·        ሮማዊያን በብዙ ስቃይ እንዲሞት የተፈረደበትን ሰው በተለይም ደግሞ አመጸኞችን ይሰቅሉ ነበር። በተለይ እንደ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ አገላለጽ ክርስቶስ ከመወለዱ ከ400 ዓመት በፊት ብዙ ሺ ህዝብ በስቅላት እንደጨረሱ የተለያየ አይነት የስቅላት ምልክቶችም አንዳሉ ይነገራል።
·        ለ እኛ ክርስቲያኖች የመዳን ምልክት ነው። ክርስቶስ የሞተው ስለ እኛ ኃጢአት ነውና የመስቀሉ ቃል የወንጌል ምልክት ሆኖልናል (1ኛ ቆሮ 1፡17-25
·        መስቀል የማስታረቅ ቃል ነው።  በሰውና በ እግዚአብሔር መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶልናልና (ኤፌ 2፤14
·        መስቀል የቅድስና ቃል ነው።  ም ዕመናን ከክርስቶስ ጋር በመስቀሉ ተባብረዋልና በመስቀሉ ኃጢአታቸውን ክደዋል፤ ከዓለም ተለይተዋል፤ በመስቀልም ትምህርት አድርገው በአዲስ ህይወት ይኖራሉ (ሮሜ 6፤4 ገላ 2፤20
·        ክርስቶስ በመስቀል  ላይ ሳለ የተናገራቸው 7 ቃላት አሉ 7 " አጽርሐ መስቀል " በመባል ይታወቃሉ።እነሱም፦
1) 
አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝማቴ 1746
2) 
አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅርበላቸውሉቃ 2334
3) 
ዛሬ በገነት ከኔ ጋር እንድትኖር በእውነትእነግርሀለሁሉቃ 234
4)
አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁሉቃ23 46
5) 
እነሆ ልጅሽ እነኋት እናትህዮሐ 1926
6) 
ተጠማሁዮሐ 1928
7) 
ሁሉ ተፈጸመ " ዮሐ 19 30
ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስትስጋው በራሱፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱንለመግለፅ የታዩ ተአምራት የሚከተሉት ናቸው፤
በሰማይ፤ /ማቴ 2429 እና 2745/

1. 
ፀሐይ ጨለመች
2. 
ጨረቃ ደም ሆነች
3. 
ከዋክብት ረገፉ
በምድር፤/ማቴ 2751_53/
1. 
የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይእስከ ታች ተቀደደ
2. 
ምድር ተናወጠች
3. 
መቃብሮች ተከፈቱ
4. 
ሙታን ተነሱ
ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በስቅላት በሞት ከፈረዱበት በኋላ ብዙ ጊዜ የሚከተሉት ነገሮች ይፈጸሙበት ነበር
1)   ከመሰቀሉ በፊት ይገረፋል (ማቴ 27፤26
2)  መስቀሉን ወይም የመስቀሉን ግንድ ተሸክሞ ከከተማ ወደ ውጭ ወዳለው መስቀያ ቦታ ይወሰዳል (ዮሐ 19፤17
3)  በምሳሌ 31፤6 የተጻፈውን በማሰብ በኢየሩሳሌም የነበረ የሴቶች ማህበር የስቃይ ማደንዘዣ መጠጥ ለሚሰቀሉት ይሰጣል (ማቴ 27፤34
4)  በመስቀል ላይ ይቸነከራል ወይም በገመድ ይታሰራል (ዮሐ 20፤25
5)  ከበደለኛው ራስ በላይ የሟቹ ወንጀል ተጽፎ ይለጠፋል (ዮሐ 19፤19
6)  የተሰቀለውን ሰው ልብስ ወታደሮች እንዲካፈሉት ያደርጋል (ዮሐ 19፤23
7)  የተሰቀለው ሰው የሚሞተው ደሙን በማፍሰስ ሳይሆን በልቡ ድካም ነው።  የሚሰቀለው ሰው ብዙ ጊዜ በሁለተኛው ወይም ሦስተኛው ቀን ይሞታል (ማር 15፤44) ወዳጆች እንዳያወርዱት መስቀሉ በወታደሮች ይጠበቃል ተሎ እንዲሞት ሲፈልጉ እግሮቹን ይሰብሩ ነበር። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ግን ጎኑን ወጉት  (ዮሐ 19፤31

ይቆየን….