ቤተ ክርስቲያን (ክፍል አንድ) - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብበት ድኅረ ገጽ ነው።

Breaking

Post Top Ad

Responsive Ads Here

Sunday, December 22, 2013

ቤተ ክርስቲያን (ክፍል አንድ)

  በዲያቆን ንጋቱ አበበ


ቤተ ክርስቲያን (ክፍል አንድ)
ቤተክርስቲያን የሚለው ኃይለ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ሦስት ዓይነት ትርጉም እናገኛለን። 
1)     ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን
2)    የክርስቲያኖች ሕብረት፤ ስብስብ ወይም አንድነት
3)    እያንዳንዱ ግለሰብ
ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን
ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መመለኪያ ቤት ስለሆነ ክርስቲያኖች ተሰባስበው የሚጸልዩበት፤ ሥርዓተ እግዚአብሔትርን የሚፈጽሙበት፤ ሕገ እግዚአብሔርን የሚማሩበት፤ ንስሐ ገብተው ሥጋወ  ደሙን የሚቀበሉበት ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ብለን እንጠራዋለን። አምላካችን  እግዚአብሔር አስቀድሞ ለሙሴ ሥሩልኝ ብሏል መካከላቸው አድር ዘንድ መቅደስ ዘጸ 25፤8።  ይህም  የሚያመለክተው መቅደሱን መሥራት ከፈቃደ እግዚአብሔር የተገኘ እንጂ ፈጠራ አንዳልሆነ ግልጽ ያደርግልናል።  የእግዚብሔር ቤተ መቅደስ የእውነት ቤት ነው። ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ በማለት ይገልጸዋል። ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን።  1ጢሞ 3፤15።  ይህ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ማደሪያ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል።  ይህ ቤት የሰማይ ደጅ ነው እንጂ ሌላ አይደለም።  ዘፍ 28፤16
እኛ እግዚአብሔር በሕንጻው ብቻ ይወሰናል አላልንም።  ነገር ግን የአምልኮቱ ቤት ነው አልን እንጂ።  ለዚህም እንዲሰራ ከእግዚአብሔር ት ዕዛዝ ተሰጠ እንጂ አንዳችም በራሱ ፈቃድ የሰራ የለም። 
ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ድንጋይ ነው፤ ጭቃ ነው አይባልም።  እቃው የተሰራበት ድንጋይ ሆነ፤ ጭቃ ሆነ፤ ሣር ሆነ የሚከብርበትና የሚመለክበት ፈጣሪ ነውና። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማቴዎስ 21፤ 7-13 እንደምናነበው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ሕጻናት ያመሰግኑት ይዘምሩ ነበር።  በዚህን ጊዜ ሕጻናቱን ዝም እንዲሉ ሲከለክሏቸውኦችም  ድንጋዮችም እንደሚያመሰግኑት ተናግሯል።  ይህም ብቻ አይደለም፤ ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ ሻጮችና ለዋጮችን አግኝቶ በጅራፍ እየገረፈ እንዳስወጣቸውና “ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ የአባቴን ቤት የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት” ዮሐ 2፤13 በማለት ገርፎ ሲያስወጣቸው እናያለን።  ታዲያ ቤቱ የማይከብርበት ቢሆን ሕንጻው የማያስፈልግ ቢሆን ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጅራፍ ገርፎ ባላስወጣቸው ነበር፤ ቤቱ ግን የ እውነት አምድና መሠረት ስለሆነ ገርፎ አስወጥቶአቸዋል።  ሁሌም እኛ ጌታን በምናከብርበት የክብር ቤቱ በመገኘት እናመልከዋለን።  እንገዛለታለን ሥጋና ደሙን በመቀበል ከእርሱ ጋር ያለንን አንድነት እንገልጻለን።
በ እግዚአብሔር ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላይ ማንም ሊናገር አይችልም።  ቤቱም የሚቃወም የ እግዚአብሔርን ማደሪያ ቤት እየተቃወመ መሆኑን እንዲያውቅ እንወዳለን።
በ እግዚአብሔር ፈቃድ እንዴት የ እግዚአብሔር መቅደስ እንደተሰራ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንመልከት፤
  • ·         ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ። 1ኛ ነገ 6፤1
  • ·         ለዘለዓለም የሚኖርበት ማደሪያ ቤት መሠራቱን ተናገረ 1ኛ ነገ 8፤1-66


 ይቆየን..........

Post Bottom Ad